የኢትዮጵያ ሙዚቃ

የመጀመሪያውን ግራማፎን ወይም የሸክላ ማጫወቻ በ፲፰፻፹፱ ዓ.ም. ሄንሪ ደ አርሊንስ እና ኒኮላስ ሊዋንቲቭ ለዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ አመጡላቸው። ይኸውም ማጫወት ብቻ እንጂ ድምጽ አይቀዳም ነበር። በኋላ ግን በዓመቱ በ፲፱፻፺ ዓ.ም. ከንግሥት ቪክቶሪያ የተላኩ የእንግሊዝ መልዕክተኞች በመጡ ጊዜ ግራማፎኑንና ድምፅ መቅጃውን ይዘውላቸው መጡ።[1]

ኢትዮጵያ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ድምፃቸው በዲስክ የተቀረፁት ዓፄ ምኒልክና እቴጌ ጣይቱ ናቸው። ዛሬ በእንግሊዝ አገር በለንደን ከተማ ብሪቲሽ ኢንስቲቲውት ኦፍ ሪኮርድ ሳውንድ በተባለው ሙዚየም ውስጥ ይገኛል።[1]